መንበረ ጵጵስና እና የሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ሕንፃ
March 9, 2018
የጽርሐ ጽዮን ፕሮጀክት በውስጡ ከሚያቅፋቸው ፕሮጀክቶች አንዱ የባሕር ዳር ሀገር ስብከት ጽ/ቤት ህንፃ ግንባታ ነው፡፡ የአርቲቸክራል ዲዛይኑ በብጹዓን ጳጳሳት አባቶች በራሳቸው ላይ በሚደፉበት የአስኬማ ቆብ ቅርጽ የተነደፈ ሲሆን፣ አሁን ተጀምረው እየተሰሩ ካሉት ፕሮጀክቶች አንዱ ነው፡፡ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ሐዋርያዊ ተልዕኮዋን በሚገባ እንድትፈጽምና ቤተ ክርስቲያኗ አገልግሎት በምትሰጥባቸው ቦታ ሁሉ ያሉ የሀገረ ስብከት ጽ/ቤቶች በተጠናከረ መንገድ መደራጀት ይኖርባቸዋል፡፡ የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ጥንታዊ የሆኑ የጣና ገዳማትን ጨምሮ ፹፭ አድባራትና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናትን የሚያስተዳድር ጽ/ቤት ነው፡፡ በመሆኑም ይህ ህንፃ ጊዜውን የሚመጥን፣ የተሟላ የቢሮና የአሰራር አደረጃጀት ያለውና የሀገረ ስብከቱን ጽ/ቤት በተለያዩ ዘርፎች የተሟላ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ክፍሎች ይኖሩታል፡፡