በዚህ በሰሜን አሜሪካ የተመረጠው አብይ ኮሚቴው በቀጥታ ተጠሪነቱ ለሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ሆኖ፤ የሥራ አስፈጻሚ ዓቢይ ኮሚቴው ደግሞ በዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው የመማክርት ጉባኤ በመሪነት የሚመራ ሲሆን ፤ በእያንዳንዱ የሥራ አስፈጻሚ አባል ስር ንዑሳን ኮሚቴዎች ተቋቁመው ንዑሳን ኮሚቴዎች በሥራ አስፈጸሚ የክፍል ኃላፊዎች ሰብሳቢነት ይመራሉ፡፡ የሥራ አስፈጻሚ ዓቢይ ኮሚቴ አባላት በሥራቸው ከ3-5 ከዚያም በላይ አባላት የያዙ ንዑሳን ኮሚቴዎች ይኖራሉ፡፡ ይህ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በየወሩ ወይም እንደ አስፈላጊነቱ አስቸኳይ ስብሰባ የሚያደርግ ሲሆን ኮሚቴዉ ፲፩ አባላት ይኖሩታል:: እነዚህም፡-
ሀ. ሊቀመንበር ረ. የሕዝብ ግንኙነት፤
ለ. ም/ሊቀመንበር ሰ. የኢንጂነሪንግ እና የግንባታ ክትትል ክፍል
ሐ. ጸሐፊ ሸ. የሕግ ክፍል
መ. የፋይናንስ ክፍል ቀ. የሚዲያና ኢንፎርሜሽን ክፍል
ሠ. የገንዘብ አሰባሳቢ ክፍል በ. የእቅድ እና ልማት ክፍል
ግብረ ኃይሎቻችን
ዶ/ር ወይንእሸት መዓዛ
አቶ ተክሌ አየለ
አቶ ሰሎሞን በቀለ
አቶ ወንድወሰን ኃይሉ
ዶ/ር ኢሳያስ አባቡ
ዲ/ን ዶ/ር ግዛቸው ጊያ
አቶ አቤል ጋሼ
አቶ ዮሴፍ ወንድሙ
አቶ ሳምሶን አግዴ
አቶ ሲሳይ ይመር
ዶ/ር እልልታ ረጋሳ
ብዙ ድጋፎች አግኝተናል
በህንጻ ዲዛይን፣ በምህንድስና፣ በሕግ፣ በአካውንቲንግ፣ በፋይናንስ፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና በሚዲያ ወዘተ በርካታ ድጋፎችን አግኝተናል። እርስዎም ይቀላቀሉን።
ብዙ ቅን ምዕመናን የተለያዩ የኮንስትራክሽን ግባቶችን ለምሳሌ አሸዋ፣ ስሚንቶ፣ ብረት ወዘተ በመለገስ ብዙ አስተዋጽኦ አድርገውልናል። እርስዎም የበኩልዎን ያበርክቱ።
በሰሜን አሜሪካ ብቻ ከተለያዩ አብያተ ክርስቲያናትና ምዕመናን ከተለያዩ ስቴቶች ወደ $400,000 የሚጠጋ የገንዘብ ድጋፍ አግኝተናል። እርስዎም የድርሻዎን ይወጡ።
በኢትዮጵያ ትጉህና ቀና የሆኑ ምዕመናን ለአሸዋ፣ ስሚንቶ እና ብረት ማመላለሻ የጭነት መኪናዎችን እንዲሁም ሌሎች ቁሳቁሶችን በመለገስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል። እርስዎም ያግዙ።
ራዕያችን እውን እንዲሆን
=> ማገዝ /መርዳት (አስተዋጽኦዎ በማበርከት)
=> በዕዉቀት
=> በዓይነት (በጥሬ እቃ ለመጀመርያ)
=> በገንዘብ
=> ከሁሉም በላይ የጸሎት ድጋፍዎን እንሻለን።