በሰሜን አሜሪካ የጽርሐ ጽዮን ፕሮጀክት አሥተባባሪ ኮሚቴ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርርስቲያን ከ፵፭ ሚሊዮን በላይ የእምነቱ ተከታይ ምእመናንና ምእመናት፣ ከ፵ ሺህ በላይ ገዳማት፣ አድባራትና የገጠር አቢያተ ክርስቲያናት፣ ከ፭፻ ሺህ ያላነሱ ካህናት እና ፮ ነጥብ ፭ ሚሊዮን የሚሆኑ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሲኖሯት፡፡ ቤተ ክርስቲያኗ በድምሩ በ፶፭ መንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት መዋቅሯን ዘርግታ ታስተዳድራለች ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከአሏት አህጉረ ስብከት አንዱ የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ነው፡፡
የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስና ጥንታውያን ገዳማትና አድባራት፤ የቤተ ክርስቲያኒቱ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶች፤ ጥንታውያን የቤተ ክርስቲያን ቤተ መዘክሮች (የቤተ ክርስቲያን ግምጃ ቤቶች)፤ የአጽመ ነገሥታት፤ የአጽመ ቅዱሳን ማረፊያ፣ በአጠቃላይ ዓለምን የሚያስደንቁ የቱሪስት መስህብ የሆኑ ገዳማትንና ወዘተ የሚገኙበትና በስሩም የሚያስተዳድራቸው ፰ የአንድነት ገዳማት፤ ፴፰ አድባራት፤ ፴፪ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት በድምሩ ፸፰፣ በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ካህናት፣የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣ምእመናንና ምእመናት የሚገኙበት ሀገረ ስብከት ነው፡፡
ስለሆነም ከላይ የተዘረዘሩት የቤተ ክርስቲያኒቱ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶች ያሏት ቤተ ክርስቲያን ታሪኳንና ትውፊቷን ጠብቃ ለቀጣዩ ትውልድ እንድታስረክብ አርቆ በማሰብ የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት የቤተ ክርስቲያንን ትውፊት የሚገልጽ ደረጃውን የጠበቀ የሕንፃ ግንባታ ሥራ ለመሥራት ”የባሕርዳር ሀገረ ስብከት ጽርሐ ጽዮን ቅድስት ማርያም ገዳም መንበረ ጵጵስና የሕንፃ ግንባታ ሥራ” በሚል ስያሜ ስለሕንፃ ግንባታው ሥራ በዝርዝር ተዘጋጅቶ ለመንግሥት ካቀረበ በኋላ ኃሳቡ ተቀባይነት አግኝቶ የሕንፃ ግንባታውን ለማስፈጸም ፵፪ ሸህ ካሬ ሜትር ስፋት ያለው መሬት ለዚሁ ሥራ የሚውል ሀገረ ስብከቱ ከመንግሥት ተረክቧል፡፡
ስለሆነም የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስና ጽርሐ ጽዮን ቅድስት ማርያም ገዳም የሕንፃ ሥራዎችን የሚያስፈጽሙ ጠቅላላ ኮምቴ ፤ የሥራ አስፈጻሚ ዓቢይ ኮሚቴ እና ንዑሳን ኮሚቴዎችን በሊቀ ጳጳሱ መሪነት አቋቁሞ የሕንፃ ሥራ አስፈጻሚ ዓቢይ ኮሚቴውም ሆነ ንዑሳን ኮሚቴዎች ሥራዎችን በሥርዓትና በተደራጀ መልኩ መምራት ይችሉ ዘንድ የሥራ አስፈጻሚ ኪሚቴ ካወቀረ በኃላ በተጓዳኝ የሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ወደ ሰሜን አሜሪካ በሥራ በመጡበት ወቅት የሰሜን አሜሪካ ሕንጻ ግንባታ እና የገቢ አሰባሳቢ የውጪ አሰባሳቢ ኮሚቴ ማዋቀር አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ፤ አብይ ኮሚቴው በዋሺንግተን ዲሲ በታሕሳስ ፳፻፲፩ ዓም ላይ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የባሕርዳር ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት የውጪው አብይ ኮሚቴ ሊቋቋም ችሏል።