የመንፈሳዊና የዘመናዊ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት
March 9, 2018
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በያዝነው የ21ኛው ክፍለ ዘመን ዘመኑን የሚዋጁ የቤተ ክስትያን ምሁራንን ማፍራት ይኖርባታል፡፡ እነዚህ የነገረ መለኮት ምሁራን የቤተ ክርስቲያኗን አስተምህሮት ከዘመናዊው ትምህርት ጋር አቀናጅተው የሚያውቁ እንዲሆኑ ሁለቱም የትምህርት ዘርፎች የሚሰጡባቸው የትምህርት ተቋማት ያስፈልጓታል፡፡ ነገረ መለኮትን ከአካዳሚክ፣ ከማህበራዊ ጉዳይ፣ ከሳይንስ፣ ከፖለቲካ ሳይንስ፣ ብሎም ከሌሎች ጉዳዮች ጋር በአንጻራዊና በተጓዳኝ የሚሰጡባቸው ኮሌጆችን የሚይዝ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በጽርሐ ጽዮን ፕሮጀክት ውስጥ ከሚታቀፉት ተቋማት አንዱ ነው፡፡ በዚህ ተቋም ውስጥ የሚሰለጥኑ ተማሪዎችና ምሁራን የቤተ ክርስቲያኗን የወደፊት በአመራርና በማኔጅሜንት በኩል በትክክል ያጠኑና የሚያስፈልገውን የዕውቀት ተዋጽኦ ማድረግ የሚችሉ እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡