ንዋያተ ቅዱሳት ማዘጋጃ
March 6, 2018
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎቷን በሚገባና በብቃት ለሕዝበ ክርስቲያኑ ማቅረብ እንድትችል በጥራትና በብቃት የተመረቱ ንዋየ ቅድሳት ያስፈልጋሉ፡፡ እነዚህ ንዋየ ቅድሳት ቤተ ክርስቲያኗ በምትፈልገው አይነት፣ ጥራትና ብዛት ማምረት እንዲቻል የንዋየ ቅድሳት ማዘጋጃ ዘመናዊ ማምረቻዎች ያስፈልጋሉ፡፡ ጧፎችን፣ ሻማዎችን፣ አልባሳትን፣ መቀደሻ የሚሆኑ ዘቢቦችን፣ የእህል ዘሮችን ለማዘጋጀት የሚያስችሉ ፋብሪካዎችን ማደራጀትና ማነጽ ያስፈልጋል፡፡ የጽርሐ ጽዮን ፕሮጀክት ከሚያቅፋቸው ፕሮጀክቶች ውስጥ እነዚህን የንዋየ ቅድሳት ማዘጋጃ ፋብሪካዎች ጉልህ ድርሻ ይኖራቸዋል፡፡ ንዋያተ ቅዱሳቱን ለማምረት የሚያስችሉ ፋብሪካዎች ተጠናቀው አገልግሎት ላይ ሲውሉ በባህር ዳር ሀገረ ስብከት ውስጥ ብቻ ሳይሆን በመላ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ ንዋየ ቅድሳትን ማምረት እንደሚቻል ይጠበቃል፡፡