ራዕይ ተልዕኮና ዓላማ

“ቀኖቹ ክፉወች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ ስለዚህ የጌታ ፈቃድ ምን እንደሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ።”ኤፌሶን ፭፥፲፮

የጽርሐ ጽዮን ፕሮጀክቶች

ትንሽ እርዳታ በማድረግ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን መደገፍ ይችላሉ። የታቀዱ ፕሮጀክቶችን ይመልከቱ!
ጥምቀተ ባህር

ጥምቀተ ባህር

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የእምነት ሥርዓት ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠው የጌታችን የአምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት በየአመቱ በጥር 11 ተከብሮ ይውላል፡፡ ይህ በዓል በባህር ዳር ከተማ እንደ ከተማው ታላቅነትና እንደ በዓሉ ክብር ደምቆ ይከበር ዘንድ ታቦታት የሚገናኙበትና የጥምቀቱ ሥርዓት የሚከበርበት ቦታ በጥሩ ሁኔታ ተሰርቶ የቤተ ከርስቲያኗን ክብር ባማከለ መንገድ እንዲጠበቅ ያስፈልጋል፡፡ ለዚህ የተመረጠውን ቦታ በትክክል አስተካክሎ ሥራ ላይ ማውል የጽርሐ ጽዮን ፕሮጀክት ከሚያቅፋቸው ፕሮጀክቶች አንዱ ነው፡፡

Donate

ቤተ መጻሕፍት

ቤተ መጻሕፍት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከምትታወቅባቸው ሀብታቶቿ መካከል ዋነኛው ለብዙ መቶ አመታት ጠብቃ ያቆየቻቸው ድርሳናትና መጻሕፍት ናቸው፡፡ በሌላው አለማት የማይገኙ ዶክሜንቶችና ጽሁፎች በገዳማትና በአብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ እነዚህን መጻሕፍትና ድርሳናት የቤተ ክርስቲያናንና ሌሎችንም የአለም ጥበባት አምቀው የያዙ ናቸው፡፡ ስለህክምና፣ ስለማዕድናት፣ ስለስነጠፈር፣ ስለከዋክብት፣ ስለትውልዶች ወዘተ አብዝተው የሚተርኩ ጽሁፎች የያዙት ጥበብ ለተማሪዎች፣ ለምሁራን፣ ለሀገር ቤትና ለአለም አቀፍ ተመራማሪዎች ተጠብቀው የሚቆዩትና ሲፈለጉ የሚገኙት በተደራጀ ቤተ መጻሕፍት ውስጥ ነው፡፡ ይህ ተቋም ዘመናዊነትን በጠበቀ መንገድ የሚደራጅ ሲሆን ዘመኑ በሚፈቅደው መንገድ የኢንፎርሜሽን ሳይንስ ጥበብ በሚፈቅደው መንገድ ተሰርቶ ጊዜውን የሚዋጅ ቤተ መጻሕፍት እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

Donate

ጽርሐ ጽዮን ቅድስት ማርያም ገዳም

ጽርሐ ጽዮን ቅድስት ማርያም ገዳም

ይህ በአሁኑ ሰዓት በግንባታ ላይ የሚገኘው የጽርሐ ጽዮን ፕሮጀክት አካል በአይነቱ ለየት ያለ ዘመናዊ የሆነ የቤተ ክርስቲያን ህንጻ ነው፡፡ ይህ ህንፃ በይዘቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የአሰራር ይዘትና ውስጣዊ ውበት የጠበቀ ሲሆን በውስጡ ባለሁለት መቅደስ ሆኖ የሚሰራ በእያንዳንዱ መቅደስ ቢያንስ እስከ አምስት መቶ ም ዕመናንን በአንድ ጊዜ ሊይዝ የሚችል ነው፡፡ ህንፃው ከአየር ላይ ሲታይ በመስቀል ቅርጽ የተቀረጸ ሲሆንምዕመኑ በአጸደ ቤተ ክርስቲያኑ ቅጽር ግቢ ውስጥ በሚኖርበት ጊዜ ጠቅላላ ልቦናውንና ውስጠቱን ከፈጣሪው ጋር በሚያስተሳስር ልዩ መስህብ ይኖረው ዘንድ ታቅዶ የተወጠነ ነው፡፡

Donate

ጽርሐ ጽዮንን እንዴት ይደግፋሉ?

0
የበጎ ፈቃደኞች ቁጥር
በየወሩ ለመስጠት
0
በሂደት ያሉ ፕሮጀክቶች
ገንዘብ ለማሰባሰብ
0
በጎ ፈቃደኞች ያበረከቱት ሰዓት
ወዳጃችን ይሁኑ
0%
የጽርሐ ጽዮን ቅድስት ማርያም ገዳም
0%
መንበረ ጵጵስና እና የሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ሕንፃ
0%
የመንፈሳዊና የዘመናዊ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት
0%
የካህናት ሁለገብ ማሰልጠኛ
0%
የግዕዝ ዩኒቨርሲቲ

እነዚህን ተስፋ ሰጭ ፕሮጅክቶች ለመደገፍ አሁኑ ይርዱ

Bitnami